በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት፡ የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
Description
የአምስተኛ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀዕ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሸክላ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ጠቅላላ ስፋቱ 4865 (አራት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ አምስት) ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች፡-
1. የጨረታውን ሰነድ በሽክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ባንክ ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ቦታወቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታውን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔሲፊኬሽን /Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 50 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ50 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።
5. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በኦ/ብ/ዞን በሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ባንክ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 4/8/2018 ዓ.ም እስከ 16/8/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ16/8/2018 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ይሆናል።
7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ17/8/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልክትይችላሉ።
9. የአካበቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ።
10. የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨረማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡- 09 32 35 64 57/ 09 23 66 11 18 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-24
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-04-25 10:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Dawa Chefa Woreda Shekla City Hall
- Bid bond: 50 በመቶ ያላነሰ
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ
- Published: Apr 14, 2026
- Posted at: 2026-04-14T14:19:04.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.