አሐዱ ባንክ አ.ማ ንብረቶችን በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር፡- 019/2018
አሐዱ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
ለሐራጅ የቀረበው ንብረት ዝርዝር መግለጫ |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር |
ሐራጁ የሚከናወንበት |
ሐራጁ የወጣው |
||||
|
የንብረቱ አይነት |
አድራሻ |
የካርታ ቁጥር |
የቦታ ስፋት |
ቀን |
ሰዓት |
||||||
|
1 |
ሲስቴክ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ወ/ሮ ክብረቴ አለማየሁ በቀለ |
መስቀል አደባባይ |
መኖሪያ ቤት |
አ. አ ከተማ፣ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07 (ቤተል አለም ባንክ)፣ የጎግል ካርታ ኮርድኔት ቁጥር 9.00476, 38.68176 |
AA000090703560 |
160 ካ.ሜ የሆነ (B+G+2) |
47,031,220.00 |
ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም |
ከ3፡00 - 4፡00 |
ለሶስተኛ ጊዜ |
|
2 |
ሲስቴክ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
እነ ወ/ሮ ክብረቴ አለማየሁ (5 ሰዎች) |
መስቀል አደባባይ |
መኖሪያ ቤት |
አ. አ ከተማ፣ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07 (ቤተል አለም ባንክ)፣ የጎግል ካርታ ኮርድኔት ቁጥር 9.00344, 38.68113 |
AA000090703347 |
120 ካ.ሜ ቪላ ቤት |
12,180,607.00 |
ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም |
ከ4፡00 - 5፡00 |
ለሶስተኛ ጊዜ |
የሐራጅ ደንቦች፡-
1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በአሐዱ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት:: ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ:: በጨረታው ተሸናፊ ለሆኑት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።
3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ብቻ ናቸው:: ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
4. የጨረታ አሸናፊ ለሆነው ተጫራች በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅደመ ሁኔታ መሠረት ብድር ሊመቻች ይችላል።
5. የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።
6. የሐራጁ አሸናፊ/ገዢ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፤ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ የግብር ግዴታዎችን ገዥው/አሸናፊው ይከፍላል።
7. ተጫራቾች የጨረታው ቀን ከመድረሱ 5 (አምስት) ቀን በፊት ከባንኩ ጋር በመነጋገር በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ በቦታው በመገኘት ለጨረታ የቀረበውን ንብረት መጎብኘት ይቻላል።
8: ማንኛውም ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰው ነው።
9. ጨረታው የሚከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 08 ፍላሚንጎ ሬስቱራንት ፊት ለፊት ሰንሻይን ህንጻ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ሐመር አዳራሽ ነው።
10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 260 223 (ሕግ አገልግሎት መምሪያ) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
አሐዱ ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-05-14
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-05-14 11:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ahadu Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 15, 2026
- Posted at: 2026-04-15T11:29:37.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.