ወጋገን ባንክ አ.ማ. ለሰጠው ብድር በእዳ ማካካሻነት ይዞት የነበረ መኖሪያ ቤት አሁን በእዳ የተረከበው በመሆኑ ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

★ Featured

Description

 የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር WB/PAF/06/26

ወጋገን ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዡ የተጠቀሰውን መኖሪያ ቤት ለሰጠው ብድር በእዳ ማካካሻነት ይዞት የነበረ እና አሁን በእዳ የተረከበው በመሆኑ ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የንብረቱ ዓይነት

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር

ቤቱ/ሕንጻው ያረፈበት ቦታ በካ.ሜ

ይዞታው ጠቅላላ ስፋት

ከተማ

ክ/ከተማ

የቦታው ልዩ ስም

የካርታ ቁጥር

G+1 መኖሪያ ቤት

ኦሮሚያ ሸገር ከተማ

ለገጣፎ ለገዳዲ

CCD (Country Club Developers) ግቢ ውስጥ

OR042030709006

26,100,000.00

ምድር ቤት 259.95 ካ.ሜ 1ኛ ወለል 220.01 ካ.ሜ ሰርቪስ ቤት 54.10 ካ.ሜ

1,022.06 ካ.ሜ

ማሳሰቢያ

1- ተጫራቾች ከየትኛውም የወጋገን ባንክ ቅርንጫፍ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ብር 345.00 (ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር) በሒሳብ ቁጥር 0736452410101 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታው ሰነድ የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ሕንጻ 3ኛ ወለል ንብረት አስተዳደር እና ፋሲሊቲስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ መግዛትና መወዳደር ይችላሉ፡፡

2- የመኖሪያ ቤቱን  ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ባንኩ በሚያወጣው መርሐ-ግብር መሰረት መጎብኘት ይችላሉ፡፡

3- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መኖሪያ ቤቱን የሚገዙቡትን ዋጋ ¼ኛ (ሃያ አምስት በመቶ) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ከነሙሉ አድራሻቸው እስከ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. 8፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ሕንጻ 3ኛ ወለል ንብረት አስተዳደር እና ፋሲሊቲስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጫራቹ ስም፣ፊርማ እና ስልክ ቁጥር መጻፍ አለበት። ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

4- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመጫረቻ ዋጋ በቀላሉ በሚጠፋ ወይም በእርሳስ መሙላት የለባቸውም። የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።

5- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፤ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ሊወጡ አይችሉም።

6- ጨረታው ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት  ሕንጻ 9ኛ ወለል በባንኩ አዳራሽ ይከፈታል።

7- የጨረታው አሸናፊ ከመኖሪያ ቤቱ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፤ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ የሚታሰብ ግብር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ካለ፣ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙ ወጪዎች፣ውዝፍ ክፍያዎች እና ሌሎች በሕግ የተወሰኑ ወጭዎች የጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል።

8- የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱን ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ ከፍሎ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለበት። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ ከፍሎ ንብረቱን የማይረከብ ተጫራች የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

9- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ማለትም እስከ 3ኛ ደረጃ ያልወጡ የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ይመለስላቸዋል።  

10- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራርያ በስልክ ቁጥር 011-5-535342 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

Ras Mekonnen Street, Wegagen Tower P.O.Box: 1018, Addis Ababa, Ethiopia

Website: www.wegagen.com Email: info@wegagen.com  SWIFT: WEGAETAA


Tender details

  • Deadline: 2026-04-27
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-04-27 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Wegagen Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 345.00 (ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር)
  • Published: Apr 15, 2026
  • Posted at: 2026-04-15T11:56:11.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders