በሀገር መከላከያ ሚ/ር የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት ማዕከል ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ፎቶኮፒ ማሽኖች እና ሌሎች እቃዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ማለትም ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ፎቶኮፒ ማሽኖች እና
ሌሎች እቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 002/2018
በሀገር መከላከያ ሚ/ር የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት ማዕከል በተለያየ ጊዜ ተገዝተው የነበሩና አሁን ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ያገለገሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ማለትም ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ፎቶኮፒ ማሽኖች እና ሌሎች እቃዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
|
ተ/ቁ |
የእቃው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
01 |
ያገለገሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ማለትም ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ፎቶኮፒ ማሽኖች፣ ጀነሬተሮች፣ የእንጨት በሮች፣ ወንበሮች እና ሌሎች እቃዎች |
ብር 5,000.00 |
ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 5፡30 ይከፈታል። |
ይህንን ጨረታ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ዜጋ የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ መጫረት ይችላል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ያገለገሉ እቃች ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን(CPO)
- ከሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ያላስያዘ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
- እቃዎቹ የሚገኙት ንፋስ ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ጎፋ ካምፕ በሚገኘው የመከ/ጠቅላይ መምሪያ ጠቅ አገልግሎት ግ/ቤት ስለሆነ እቃዎች
- ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳት በአካል መጎብኘት ከፈለጉ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 – 5፡30 እና ከሰአት ከ 7፡30 – 9፡30 ድረስ ማየት ይችላሉ።
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው እለት ድረስ ዘወትር
- በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ ጦር ኃይሎች ፈት ለፊት በሚገኘው የመከ ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ህንፃ
- ብሎክ C 4ኛ ፎቅ ጠቅመም ፋይ ስራ አመዳይ ት ፋይናንስ ቡድን በመቅረብ ለዚህ ጨረታ በአማርኛ የተዘጋጀውን ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል ገዝተው መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ሳጥን የሚዘጋጀው ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የመከ/ ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ህንፃ ብሎክ C 4ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ይሆናል።
- የመጫረቻ ሰነድ ማስገባት የሚቻለው ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በጨረታ መክፈቻው እለት ሆኖ በእለቱ 5፡00 ተዘግቶ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰዓቱ ከ2፡30 - 5፡00 ድረስ ሲሆን ጨረታው ይከፈታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ከውድድሩ ቢወጡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ሲሆኑ የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ ከፍሎ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ንብረቱን ማንሳት አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ አድራሻ አ/አበባ ጦር|ኃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው
የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ህንፃ ብሎክ ሲ 4ተኛ ፎቅ የግዥ ቡድን ስልክ ቁጥር 011 317 2009 ጠይቀው መረዳት ይችላሉ።
በሀገር መከላከያ ሚ/ር የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-05-04
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-05-04 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በሀገር መከላከያ ሚ/ር የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት ማዕከል
- Bid bond: 5,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 16, 2026
- Posted at: 2026-04-16T08:26:03.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.