የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ዕቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ እስፔርፓርት የጽዳት ዕቃ እና ልዩ ልዩ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ
- የተለያዩ አልባሳት፣
- ኮንስትራክሽን፣
- ኤሌክትሮኒክስ፣
- የቤት ዕቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣
- ጫማዎች፣
- ምግብ ነክ፣
- እስፔርፓርት
- የጽዳት ዕቃ እና
- ልዩ ልዩ በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች በቀን 13/08/2018 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች -
- ለግልፅ እና ለሐራጅ ጨረታ በዘርፍ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
- ለሐራጅ ጨረታ ለመሳተፍ ዕቃውን ለመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ማቅረብ የሚችል፣
- ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ዕቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ማቅረብ የሚችል፤
- ለሐራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፣
- ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገፃለን ፣
- ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ዕቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆነ አለበት፤
- ዕቃዎቹን አሽንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፤
- በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፣
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል።
- ተጫራቹ ዕቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
- ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ ከቀን 13/08/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በቀን 15/08/2018 3:45 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው በቀን 15/08/2018 ከረፋዱ 4:15 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤
N.B፦ አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤
ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-23
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: Apr 16, 2026
Categories
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsBuilding ConstructionConstruction and Water WorksComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesHome Appliance and SuppliesFurniture and FurnishingCleaning and Janitorial Equipment and ServiceOther SalesSales, Disposals and ForeclosureSpare Parts and Car Decoration MaterialsFood Items and DrinksFood and BeverageDisposal SaleAmharic2merkatoEthiopian Customs CommissionSomali
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.