ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ የሚረዱ ቁሳቁሶች እና የማጣቀሻ መጽሐፍት (ለተማሪዎች ሽልማት የሚውል) ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ እና ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 16 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ "በ16 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል የሚል ሙሉ ትኩረቱን በትምህርት ጥራት ላይ ያደረገ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ድርጅታችን ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት / ECD / ለነዚህ አጋር ትምህርት ቤቶች የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ለማሻሻል እና ኮከብ ተማሪዎችን ለማበረታታተ የሚውሉ  ግብዓቶችን ለመግዛት አቅዷል፡፡ በመሆኑ የሚከተሉትን ቁሳቁሶችን ለማቅረብ የምትፈልጉ እና መስፈርቶቹን የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የሚገዙት ቁሳቁሶችም የሚከተሉት ናቸው።

ሎት

ዘርፍ

ዝርዝር መረጃ

ምርመራ

1

የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ የሚረዱ ቁሳቁሶች

ዝርዝር መረጃው በጨረታው ሰነድ ውስጥ ገኙታል

 

2

የማጣቀሻ መጽሐፍት(ለተማሪዎች ሽልማት የሚውል)

ዝርዝር መረጃው በጨረታው ሰነድ ውስጥ ገኙታል

 

 ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  1. ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ዝርዝር መረጃው በጨረታው ሰነድ ውስጥ ገኙታል
  4. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ቁሳቁሶቹን በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሠረት ማቅረብ የሚችሉ፣
  6. የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ የሚጠቀሙ ከሆነ በብርሃንና ሰላም የታተመ የኪው አር ኮድ ያለው ደረሰኝ የሚያቀርቡ
  7. ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው ስቶር ማድረስ የሚችሉ፣

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከድርጅታችን የጨረታ ሰነዱን በነጻ በመውሰድ ቁሳቁሶቹን የምታቀርቡበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባትና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

አድራሻ፦ ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት / ECD/

አዲስ አበባ፣ ቦሌ አለም ህንፃ 7ኛ ፎቅ

ስልክ፦ 0982 88 2826

  1. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ግብዓት ከማቅረባቸው በፊት ሳምፕል ማሳየት ይኖርባችኋል።
  2. ተጫራቾች የምታቀርቡት ዋጋ ሻትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ማሳየት ይኖርባችኋል፡፡ በትክክል ካልተገለጸ ቫት እንደተካተተ ተደረጎ ይቆጠራል።
  3. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ማስታወቂያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲቨሎፕመንት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-22
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-04-22 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Center for Development (ECD)
  • Buyer address: Bole Road Haile Alem Building, 7th Floor
  • Published: Apr 17, 2026
  • Posted at: 2026-04-17T07:43:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders