የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የኃይጅንና ሳንቴሽን ሥራዎችን ለማጠናከር የሚያገለግል የቆሻሻ ማስቀመጫ/DUST BIN/ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የኃይጅንና ሳንቴሽን ሥራዎችን ለማጠናከር የሚያገለግል የቆሻሻ ማስቀመጫ/DUST BIN/ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ለወዳደር የተጋበዙ መሆኑን እያሳወቅን፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ።
  3. ከላይ በተራ. ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ፤ ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ጠቅላላ ዋጋ ከ 500,000.00/አምስት መቶ ሽህ ብር/ መብለጥ የለበትም።
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
  8. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም በ 8:30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
  9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  10. ቢሮው የግዥዉን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  11. የጨረታዉ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈውን የኃይጅን እና ሳኒቴሽን እቃዎች የጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው ስርጭት (ድልድል መሰረት ለጤና ተቋማት ማቅረብ አለበት።
  12. በጨረታው የተወዳደረ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር / በመክፈል ከቢሮው የሰነድ ሽያጭ ከፍል መውሰድ ይችላል።
  13. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ስለ ጨረታዉ መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ስልክ ቁጥር 058-222-1127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-11
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም በ 8:30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-11 15:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም በ9:00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Health Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 26, 2026
  • Posted at: 2026-04-27T09:54:25.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders