ከምባታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የመኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አውጥቷል
Description
በድጋሚ 2ኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ከሣሽ ከምባታ ዞን ፍትሐብሔር ጉዳዮች ዐ/ህግ እና በአፈፃፀም ተከሣሾች ıኛ) ሠላሙ ዳንኤል፣ 2ኛ) አስፋው ሀንዴቦ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ ይህ ፍ/ቤት በመ.ቁ.12015 በቀን መጋቢት 14/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በፍርድ ባለመብትና በፍርድ ባለዕዳዎች መካከል ስላለው የሙስና ወንጀል ክስ ጉዳይ 1ኛ) ባለዕዳ ሣሙኤል ዳንኤል ብር 22,955,515.30 (ሃያ ሁለት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ሃምሣ አምሥት ሺህ አምሥት መቶ አሥራ አምሥት ብር ከሠላሣ ሣንቲም) እንድከፍል የተወሰነበት በመሆኑ በፍርድ ባለዕዳ ስም ሠላሙ ዳንኤል ባለቤት ወ/ሮ ሰላምነሽ ለቴቦ ስም በከምባታ ዞን ሺንሺቾ ከተማ ተመዝግቦ ያለ በአዋሳኞች በምሥራቅ ታመነ ፈለቀ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን አድነው እና በደቡብ ሀብቴ ታገሠ መሃል ያለው ይዞታ መሬት ስፋቱ 140 ካሬ ሜትር የሆነ የቦታው አገልግሎት መኖሪያ የሆነ በጨረታ መነሻ ዋጋ አንዱ ካሬ ብር 142 (አንድ መቶ አርባ ሁለት ብር) የ140 ካሬ መነሻ ዋጋ 19,880 (አስራ ዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ ብር) ሲሆን ታክስን ሳይጨምር በሊዝ ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ በሀራጅ እንዲሸጥ በተወሰነው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ 1,988 (አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር) በፍ/ቤቱ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ሥራ ሂደት ተጫራቾች በማስቀመጥ መወዳደር ይችላሉ።
ይህ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 12015 በቀን 14/07/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት የፍርድ ባለመብትና የፍርድ ባለዕዳዎች መካከል ስላለው የሙስና ወንጀል ክስ ጉዳይ የፍርድ ባለዕዳ አስፋው ሀንዴቦ 4,153,607(አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሃምሣ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር) የተወሰነ በመሆኑ የፍርድ ባለዕዳው ስም በከምባታ ዞን ሺንሺቾ ከተማ ተመዝግቦ የሚገኝ በአዋሳኝ በምሥራቅ ታመነ ፈለቀ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን አድነው እና በደቡብ ሀብቴ ታደሰ በሚያዋስኑት ስፋቱ 350 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ያለ መኖሪያ ቤት እና ተያይዞ ያሉ ቤቶች መነሻ ዋጋ ታክስን ሳይጨምር፡- መነሻ ዋጋ ግምት ብር 1,870,000 (አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሰባ ሺህ ብር) ፍ/ቤቱ ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ ይፈልጋል። ጨረታ ማስከበሪያ ብር 187,000(አንድ መቶ ሰማኒያ ሰባት ሺህ ብር) በፍ/ ቤቱ ግ/ፋ/ን/አስ/ሥራ ሂደት በማስቀመጥ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
ይዞታው የሚገገኝበት አድራሻ |
የቦታው ሰዓት ካ.ሜ
|
የቤቱ አገልግሎት
|
የፍርድ ባለዕዳ እንዲከፍል የተወሰነበት
|
የንብረቱ ባለቤት ስም |
ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ጨረታ መነሻ ዋጋ ታክስ ያለበት |
ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
ሺንሺቾ ከተማ አስ/ር |
140 |
መኖሪያ
|
22,955.517.30 (ሃያ ሁለት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ሃምሣ አምሥት ሺህ አምስት መቶ አሥራ ሰባት ብር ከሠላሣ ሣንቲም) |
ሰላምነሽ ለቴቦ |
|
19,880 (አሥራ ዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ ብር) |
1,988.00 (አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር) |
ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በከምባታ ዞን ከፍ/ፍ/ ቤት ፍትሐብሔር ችሎት አዳራሽ |
|
2 |
ሺንሺቾ ከተማ አስ/ር |
350 |
መኖሪያ ቤት
|
4,153,607(አራትሚሊየን አንድ መቶ ሃምሣ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር |
አስፋው ሀንዴቦ
|
|
1,870,000 አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሰባ ሺህ ብር) |
187,000 (አንድ መቶ ሰማኒያ ሰባት ሺህ ብር) |
ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በከምባታ ዞን ከፍ/ፍ/ ቤት ፍትሐብሔር ችሎት አዳራሽ |
ተጫራቾች መከተል ያለባቸው ደንቦች -
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 31ኛው ቀን ላይ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ፡- በከምባታ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር ችሎት አዳራሽ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ግንቦት 10/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት።
- ሐራጁን ቤት ተጫራቾች ሲፈልጉ ከሣሽ ያስጎበኛል።
- ጫራቾች መነሻ ዋጋውን 10% አስይዘው ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ።
- ጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱን ከፍርድ ቤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃለው ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ደግሞ ያስያዙት ይመለስላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዘ ማንኛውንም ለመንግሥት የሚከፍሉ ከፈያዎች ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ክፊያዎች ገዥ ይከፍላል።
- ንብረቱ በገዥ ስም እንዲዘዋወር ፍ/ቤቱ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
- ለጨረታው የቀረቡትን ቤቶች ይዞታ መሬት በሥራ ሰዓት ማየት ይቻላል።
መረጃ ለማግኘት የፍ/ቤቱ ስልክ ቁጥሮች የዳኞች ጽ/ቤት፡- 046 554 0541
የሬጅስትራር ጽ/ቤት- 046 554 0858 መጠቀም ይቻላል።
የከምባታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-18
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-18 10:00
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Kembata Zone High Court
- Bid bond: 10%
- Published: Apr 18, 2026
- Posted at: 2026-04-18T08:13:38.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.