አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ባለ 10 ወለል (G +10) ዘመናዊ ህንጻ በሙሉ ወይም በከፊል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 006/2018
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ባለ 10 ወለል (G +10) ዘመናዊ ህንጻ በሙሉ ወይም በከፊል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብቻ ጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነዱን አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-06 ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለ።
2. በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።
3. አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ማስፈርና መጨረሻ ቦታ ላይ ፊርማና ማህተም በመምታት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 አስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ጠቅላላ የኪራይ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከመወዳደሪያ ፖስታ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
7. ተጫራቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከሰዓት በኋላ 7፡30 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል ።
9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-06 ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 11 92 45 97
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-05-01
- Bid closing time: 13:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 7፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-01 13:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 7፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 19, 2026
- Posted at: 2026-04-20T08:22:04.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.