አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አማ/ የስጠው ብድር ባለመከፈሉ በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) 216/92 መሠረት በእዳ ማካካሻት የወረሳቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
  • ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ንብረቶቹ በሚገኙበት የባንኩ አዳማ ዲስትሪክ እና አዲስ አበባ ሰሜን ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ሕንጻ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መውሰድ ይቻላል።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተጫራቾች ንብረቱን ለመግዛት የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፁ ላይ ካሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ በስም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታው መካሄጃ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ጨረታው በሚካሄድበት አዳማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በሰንጠረዥ በተገለጸው ቦታ ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 አስከ 5፡30 ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር 115% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ገዢ ይከፍላል:: የሊዝ ክፍያ ውል ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • ሰተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-26 45 94 / 0918 - 778427 አዲስ አበባ ወይም 0912 83 52 45 አዳማ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ሙሉ ስም

የመያዣ ሰጭው ስም

የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት

የቦታው ስፋት

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ጨረታው የወጣበት ጊዜ

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ

1

ኢብራሂም መሀሐመድ ኑር

ይድነቃቸው መንበሩ

 

ሆቴል

 

820 ካሜ

 

804/07

 

ኦሮሚያ // ኦለንጭቲ ከተማ

16,662,424.75

 

በድጋሚ

 

ሚያዚያ 21 ቀን 2018 . . ከተማ ሰሜን ሆቴል ጎን በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 6 ፎቅ እና ንብረቶቹ በሚገኙበት አዳማ ዲስትሪክት /ቤት

2

ኢብራሂም መሀሐመድ ኑር

ዮርዳኖስ ንጉሴ

መኖሪያ ቤት

 

188 ካሜ

 

0264/08

 

ኦሮሚያ // ኦለንጭቲ ከተማ

2,973,853.00

 

በድጋሚ

 

‘’

3

ዳንኤል መብራቱ

 

ተበዳሪው

 

መኖሪያ ቤት

 

400 ካሜ

 

57/34/1892

ኦሮሚያ // መተሐራ ከተማ

709,845.00

 

በድጋሚ

‘’

4

አል-ባብ ትሬዲንግ /የተ/የግ/

ፈትያ ነጂ

 

የንግድ ቤት

 

400 ካሜ

 

737990/98

ኦሮሚያ // አዳማ ከተማ

15,063,471.94

 

በድጋሚ

‘’

5

ጂዲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ /የተ/የግ/ማ

 

መሐመድነር አሊ

 

መጋዘን

 

1736 ካሜ

1081/93

ኦሮሚያ // አዳማ ከተማ ቀበሌ 01

25,856,220.81

 

በድጋሚ

‘’

6

አቤል ቃለአብ

 

ሰብለወርቅ ግርማ

 

ጅምር ሕንጻ

 

325.31

ETH0000

10254763

አደማ ከተማ ጎሮ ቀበሌ

10,045,022.39

 

በድጋሚ

‘’

 


Tender details

  • Deadline: 2026-04-29
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-04-29 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Apr 19, 2026
  • Posted at: 2026-04-20T08:28:01.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders