የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ 3ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 130 እና ለንግድ/ ለድርጅት 15 ቦታዎች በድምሩ 145 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት በ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 130 እና ለንግድ/ ለድርጅት 15 ቦታዎች በድምሩ 145 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ/ድርጅት/ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ቀበሌ 08 ከአዲሱ መሬት መምሪያ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 310 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10/ አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡00 ሰዓት ብቻ በቢሮ ቁጥር 310 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይሆናል።
ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ይሆናል። ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበትን ቦታ በተመለከተ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ እና በBahirdar City Communication የፊስ ቡክ ገፅ ማግኘት ይቻላል።
መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት
መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-04-30
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-01 10:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: Apr 19, 2026
- Posted at: 2026-04-20T13:10:07.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.