በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ ያስገነባው የጋራ መኖሪያ ቤት ቃሊቲ ሁለት (2) ተብሎ የሚጠራው ሳይት አጠገብ ባለ G+3 ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር መ.ሠ.ፋ/ብ.ግ.ጨ-018/2018
በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ ያስገነባው የጋራ መኖሪያ ቤት ቃሊቲ ሁለት (2) ተብሎ የሚጠራው ሳይት አጠገብ ባለ G+3 ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
- ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ባለ G+3 ሕንጻ ኪራይ
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገስፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው የምትሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. ተጫራቾች ሊከራዩ በፈለጉት ቤት በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ/ VAT Registration Certificate/፤ እና የቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መ.ሰ.ፋ ግዥ ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 015 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላለ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም የወሩን የኪራይ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሃያ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ስም አሰርተው በመስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ ተለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 015 በመምጣት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት መ.ሰ.ፋ ግዥ ቡድን ይከፈታል።
6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።
7. በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
8. ፋውንዴሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው ላንድ ማርክ ሆስፒታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር 0115 572 752
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
Tender details
- Deadline: 2026-05-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-05 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Forces Foundation
- Buyer address: ከቄራ ወደ ሜክሰኮ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T07:52:39.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.