የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት የቢሮ ኪራይ እስከ ሁለት አመት በሚደርስ ውል በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- ኢስአ/ግጨ/001/2018

መ/ቤታችን በ208 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የግዥው ዓይነት መግለጫ

የጨረታ ሠነድ መግዥያ ዋጋ (የማይመለስ)

የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር

 

የቢሮ ኪራይ እስከ ሁለት አመት በሚደርስ ውል

200.00

5,000.00

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

1. የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ደብረብርሃን ቅ/ፅ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ በመምጣት 200 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።

2. የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ፍቃድ የለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ወይም የቲ.ኦቲ ተመዝጋቢ የሆነ፣ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችል።

3. በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ደብረብርሃን ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 5,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የቢሮ ይዘት ለተጫራቾች በሚሸጠዉ የጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።

5. ሠነዳቸውን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግንቦት 04 ቀን /2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ግዥና ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል።

6. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ደብረብርሃን ቅ/ፅ/ቤት

ስልክ 0925513431/0912335594

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-05-12 14:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Ethiopian Statistics Service
  • Buyer address: ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ
  • Bid bond: 5000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 20, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T08:26:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders