በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት 24 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8/1 መሰረት በ2018 በጀት አመት ለ2ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ቤት ብዛት 23 ፣ለማንፈክቸሪንግ ብዛት 1 በድምሩ 24 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡

2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት ይችላሉ፡፡

3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡

4. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልሆነም ተወካዮችም ሆነ ግለሰቦቹ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በነ/መ/ከ/አስተዳደር ቀበሌ 03 ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ይሆናል፡፡

5. ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡

6. ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሃሳቦችን (ህጎችን) ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጽ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 01 92 ወይም 058 445 13 60 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-30
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡00
  • Bid opening: 2026-05-01 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በ3፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Nefas Mewucha City Administration Urban and Infrastructure Bureau
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 20, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T10:21:21.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders