የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐብሔር ችሎት የቤት የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በባለመብት ወ/ሮ ዱኒያ መሀመድ አሊ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ዳዊ አህመድ አሊ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 92353 የተስጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በፍርድ ባለዕዳ ስም በለገሀራ ገጠር ቀበሌ አስተዳደር በቢጫ ካርድ ቁጥር 15799 በቤት ቁጥር 037 የተመዘገበው ቤትና ይዞታ በሃራጅ ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 403,100.99 /አራት መቶ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ብር 99/100/ በሆነ ዋጋ በሃራጅ ሽያጭ እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል፡ ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 4፡30 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሔድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡35 እስከ 5፡20 ባለው ጊዜ ይከናወናል። በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ማንኛውም ተጫራች ለሃራጅ ጨረታው ከመዝገቡ በፊት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ቀድሞ በCPO በባንክ አስይዘው እንዲመዘገቡ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ በCPO ወይም በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው፡፡ ቀሪውን 3/4ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐብሔር ችሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-23
  • Bid closing time: 11:20
  • Bid opening: 2026-05-23 11:20
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 22, 2026
  • Posted at: 2026-04-25T08:13:27.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders