በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቀራንዮ ጤና ጣቢያ የጠቅላላ ጥገና እና የፅኅፈት መሳሪያዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኮ/ቀ/ክ/ከ/ቀ/ጤ/ጣ/ በ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፤
- ሎት 1. የጠቅላላ ጥገና
- ሎት2. የፅኅፈት መሳሪያዎች
በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንከ ሲፒኦ ሎት1፤ 9,000 ሎት2 10,000.00 ማስያዝ የሚችል።
- የጨረታው አሸናፊ ድረጅት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል።
- የጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጃችሁ በሙሉ መወዳደር የምትችሉት ባመረታችሁት ዕቃ ብቻ ሲሆን አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ በአደራጃችሁ ፅ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- አንዱ በሰጠው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- ተጫራቾች ሰነድ ለማስገባት ሲመጡ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን መሸጫ በየሎቱ ዋጋ ብር 300.00 ነው።
- ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችል ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በተቋሙ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 59 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት። ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ማሳሰቢያ ፤
- ጤና ጣቢያው በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጤና ጣቢያው ለጨረታ አሸናፊው ውል ከመዋዋሉ በፊት 20% ወደላይ መጨመር 20% ወደታች መቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተወዳዳሪዎች ለአሸነፉት ዕቃ ባስገቡት ናሙና መሠረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የሚቀርቡትን ዕቃዎች በተቋሙ ጥራት ኮሚቴ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።
አድራሻ ፤
ከጦር ኃይሎች ወደቀራንዮ የሺደበሌ በሚወስደው መንገድ ወረዳ 08 ፅ/ቤት በስተጀርባ ቀ/ጤ/ጣቢያ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፤ 011 383 9040
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቀራንዮ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-07 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቀራንዮ ጤና ጣቢያ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Apr 25, 2026
- Posted at: 2026-04-25T08:46:57.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.