የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

የመያዣ ንብረቱ መለያ

የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)

 

የጨረታው ቀን

 

አድራሻ

የይዞታ ማረጋገጫ ቁጥር

የይዞታው ስፋት (ካሜ)

የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎቱ

1

ሪፍት ቫሊ እና ሆስፒታል /ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ኃ/የተ/የግ/

/ ዳንሴ ጉርሙ

አዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ /ከተማ ወረዳ 07

 

AA000100704105

 

2,041

 

ለንግድ አገልግሎት የሚዉል ሕንፃ

143,983,491.2

 

18/9/2018 . ከጠዋቱ 300-400

 

2

አቶ አሰፋ ዱካሌ

ሻሽሞ ዱካሌ ዋቀዮ

 

ሐዋሳ ከተማ መነኻሪያ /ከተማ

 

በቀድሞ 5208 በአዲሱ SN001010806078

 

750

 

ለድርጅት

 

10,813,576.57

 

18/9/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 400-500

 

3

አቶ አብደላ ገነሞ

ተበዳሪው

ኦሮሚያ ክልልሻሸመኔ ከተማ አሌሉ ቀበሌ

9072

 

350

 

መኖሪያ ቤት

 

4,454,359.55

 

18/9/2018 . ከጠዋቱ 300-400

 

4

አቶ አብደላ ገነሞ

አቶ በሺር ገመዳ

ኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ

H46

275

 

መኖሪያ ቤት

1,527,863.26

 

18/9/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 400-500

 

5

አቶ አብደላ ገነሞ

አቶ ዳንኤል ወልዴ

 

ኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ

9081

 

350

 

መኖሪያ ቤት

4,583,655.51

 

18/9/2018 . ከጠዋቱ 500-600

 

6

አቶ ዳዊት ታደሰ ሞላ

 

እነ መክብብ ደምሴ ሽበሽ

በኮምቦልቻ ከተማ፣ ቀበሌ 04

 

3457 ሊዝ/ኮ/ቴ አገ/ቀ04/2002

 

2500

 

የመኖሪያ ህንፃ

 

9,480,116.30

 

18/9/2018 . ከጠዋቱ 300-400

በመሆኑም 

  1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡

2. በተራ ቁጥር 1-2 የተገለጹት ንብረቶች ጨረታ የሚከናወነዉ አምባሳደር አካባቢ በሚገኘዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 42ኛ ፎቅ በሚገኘዉ አዳራሽ ቁጥር 4203 ነው፤ ከተራ ቁጥር 3-5 የተገሰፁት ንብረቶች ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን፤ በተራ ቁጥር 6 ላይ የተገለጸው ንብረት ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነዉ።

3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።

4. ለጨረታ ከቀረቡ የመኖሪያ ቤቶች ዉጪ የሆኑ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።

5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።

6. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።

7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

8. ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ

በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ. 011-113-0508 ወይም አምባሳደር አካባቢ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት 42 ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።


Tender details

  • Deadline: 2026-05-26
  • Publishing entity: Commercial Bank of Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 26, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders