ወጋገን ባንክ አ.ማ. ለንግድ አገልግሎት የሚሆን ደረጃቸውን የጠበቁ ኮንዶሚኒየም የንግድ ቤቶች ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የንግድ ቤት ኪራይ ጨረታ ቁጥር WB/PAF/08/26

ወጋገን ባንክ አ.ማ. ለንግድ አገልግሎት የሚሆን ደረጃቸውን የጠበቁ ኮንዶሚኒየም የንግድ ቤቶች ለማከራየት ይፈልጋል::

ስለሆነም ከዚህ በታች የቤቶቹ አድራሻ፣ ስፋት እና የመወዳደሪያ መነሻ ዋጋ በዝርዝር የተገለጹ ሲሆን መስፈርቶችን ለሚያሟሉ እና ለመከራየት ፍላጎት ላላቸው ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በዚህ ውድድር እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል::

.

ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ

ጠቅላላ ስፋቱ በካሬ ሜትር

በካሬ ሜትር .. ጨምሮ

የባንኩመነሻ ዋጋ ..ታን ጨምሮ ወር

1

ክራውን ኮንዶሚኒየም B-02 የቤት ቁጥር C-B02/SH/08

30.65

1,500.82

ብር 46,000.00

2

ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም B-625 የቤት ቁጥር B-652/5

119.49

594.19

ብር 71,000.00

ማሳሰቢያ፡-

1- ተጫራቶች የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ያለው/ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል::

2- ተጫራቾች ከየትኛውም የወጋገን ባንክ ቅርንጫፍ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ብር 345.00 (ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር) በሒሳብ ቁጥር 0736452410101 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታውን ሰነድ የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ሕንጻ ስታዲዮም ፊት ለፊት 3 ወለል ንብረት አስተዳደር እና ፋሲሊቲስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና መወዳደር ይችላሉ:: ባንካችን ይህንን የንግድ ቤት የሚያከራየው ለረጅም ጊዜ ውል ከተከራዮቹ ጋር ዘላቂና አስተማማኝ አጋርነትን ለመፍጠር በማሰብ ነው::

3- የሚከራዩትን ንግድ ቤቶች ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ባንኩ በሚያወጣው መርሐ-ግብር መሰረት ቤቶቹ የሚገኙበትን ሁኔታ መመልከት ይችላሉ:: የንግድ ቤቶቹ የሚገኙት አራብሳ ኮንዶሚኒየም ወጋገን ባንክ ቅርንጫፍ አጠገብ እና ክራውን ኮንዶሚኒየም ወጋገን ባንክ ቅርንጫፍ አጠገብ ነው፡፡

4- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ከመነሻ ዋጋው 1/4ኛ (ሃያ አምስት በመቶ) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ከነሙሉ አድራሻቸው እስከ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም. 3፡30 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንጻ 3ኛ ወለል ንብረት አስተዳደር እና ፋሲሊቲስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጫራቹ ስም፣ፊርማ እና ስልክ ቁጥር መጻፍ አለበት። ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

5- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ በቀላሉ በሚጠፋ ወይም በእርሳስ መሙላት የለባቸውም፡፡ የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።

6- ጨረታው ግንቦት 03 ቀን ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ 3ኛ ወለል ላይ ንብረት አስተዳደር እና ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል::

7- ተጫራቶች ከባንኩ መነሻ ዋጋ በታች የመወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት አይችሉም::

8- ተጫራቶች የሚቀርቡት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል::

9- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም:: ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፤ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ሊወጡ አይችሉም::

10- የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱን ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የቅደመ ክፍያ እና ተቀማጭ የአንድ ወር ኪራይ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ያላደረገ ተጫራች የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::

11- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ማለትም እስከ 3ኛ ደረጃ ያልወጡ ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለጸ በኋላ እና የጨረታው አሸናፊ ሙሉ ክፍያውን ከፍሎ ሲያጠናቅቅ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ይመለስላቸዋል ::

12- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::

ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራርያ በስልክ ቁጥር 011-5-58-12-69 / 0115-52-38-00 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

Ras Mekonnen Street, Wegagen Tower P.O.Box: 1018, Addis Ababa, Ethiopia

Website: www.wegagen.com Email: info@wegagen.com SWIFT: WEGAETAA


Tender details

  • Deadline: 2026-05-11
  • Publishing entity: Wegagen Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 345.00 ብር
  • Published: Apr 26, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders