በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደ ውሃ ከተማ ቴ/ሙ/ማ ኮሌጅ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት የማሰልጠኛ ማቴሪያሎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደ ውሃ ከተማ ቴ/ሙ/ማ ኮሌጅ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት የማሰልጠኛ ማተሪያሎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን፤- ሎት 1 እስቴሽነሪ እቃ ሎት 2 ጋርመንት ሎት 3 ኮንስትራክሽን ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 5 የእንስሳት ህክምና ማሰልጠኛ ማቴሪያሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸው
3 የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው። በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታው ላይ የሚወዳደሩበትን የግዥው አይነትና ሎት በመፃፍ በገንዳውሃ ከተማ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ለጨረታ ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. የጨረታ ሰነዱን ከገ/ውኃ ከተማ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ በብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ሁኖ በ22ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ። ጨረታዉ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዝ/ውኃ ከተማ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 03 በግልፅ ይከፈታል።
8. ስለጨረታው አጠቃላይ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
9. አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን በገንዳ ውሃ ከተማ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች ሰነዱን በሚሞሉበት ሰዓት ስርዝ ድልዝ መኖር የሌለበት ሲሆን የእቃው ናሙና ቢሮ ቁጥር 03 በግንባር በመቅረብ ማየት ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን በሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
12. ጨረታው በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በሞላ ስለሆነ ከመጫረቻ የዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ክፍት ማድረግ የለባችሁም በተጨማሪም የእቃዎች ብዛት ከበጀት አንፃር ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
13. ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካለ በጽ/ቤቱ የውስጥ ሰሌዳ የምናሳውቅ መሆኑ
14. የአብክመ ግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1/2003 እና በተጨማሪ በቢሮው የወጡ የመመሪያ ማሻሻያዎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል።
15. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
16. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 331 0415 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ።
17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ማሳሰቢያ ፡- በተጨማሪ በ05/08/2018 ዓ.ም የወጣውን አዲስ ዘመን ጋዜጣ መመልከት ይቻላል።
በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንዳ ውሃ ከተማ ቴ/ሙ/ማ ኮሌጅ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/በድን
Tender details
- Deadline: 2026-05-18
- Publishing entity: West Gonder Zone Genede Wuha City FEDB
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Apr 26, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.