አብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት የደብረ ማርቆስ ምድብ ችሎት የመኖሪያ ቤት የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

አፈ/ከሳሽ 1 አየሁአለም ይስማው 2. ማርታ ታደሰ 3. ህይወት ታደሰ እና በአፈ/ተከሳሽ 1. አበበ ታደሰ 2. ንብረቴ ታደሰ 3. ትእግስት ታደሰ 4. እድሜአለም ታደሰ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ፡- በደብረ ማርቆስ ሪጅኦ ፖሊታንት ከተማ አስተዳደር በአብማ ክ/ከተማ ቀበሌ 13 በምስራቅ እምሬ እማምነው፣ በምእራብ መንገድ፣ በሰሜን ትርፍ ቦታና መንገድ፣በደቡብ አየሁአለምይስማው የሚያዋስኑት 250 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት መነሻ ዋጋው 1,512,612.98(አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ አስራ ሁለት ብር ከ98/100) የሆነውን ፍ/ቤቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ጨረታው ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ቤቱ ባለበት ቦታ በጨረታ ይሸጣል።

ስለዚህ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከላይ በተገለጸው ቦታ እና ሰዓት የጨረታውን መነሻ 1/4ኛ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ሰነድ ወይም CPO በማስያዝ እንዲሁም ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ መጫረት የሚችል መሆኑን ፍ/ቤቱ ይገልፃል።

አብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት የደብረ ማርቆስ ምድብ ችሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-27
  • Publishing entity: የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የደብረማርቆስ ምድብ ችሎት
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 26, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders