Land lease and real estate
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
Description
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ወሎ ዞን የአጅባር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት አመት ለ2ኛ ጊዜ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት፤ የመኖሪያ 12 ቦታዎች ማስተላለፍ የሚፈልግ ሲሆን፤ አንዱ ቦታ G+1 ሊሆን የሚችል ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
1. ከሚያዘያ 1/08/2018 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ 400 ብር የማይመለስ በመክፈል እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 15 በመቶ በማስያዝ በማዘጋጃ ቤቱ ቅጥር ግቢ፤ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመምጣት ዘወትር በስራ ሰአት ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከሚያዚያ 01/08/2018 እስከ ሚያዚያ 15/08/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
3. ጨረታው የሚዘጋው ሚያዚያ 15/08/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
4. ጨረታው የሚከፈተው ሚያዚያ 16/08/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በማዘጋጃ ቤቱ ግቢ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
5. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በስ/ቁ 033 441 0582 /09 14 06 56 11 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የአጅባር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Publishing entity: Ejebar City Council
- Bid bond: 15%
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
- Published: Apr 27, 2026