የይዞታው ስፋት በካርታቸው መሰረት 536.85 ካ.ሜ. የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አቶ አብርሀም ቢርመታ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ አሰለፈች ቢርመታ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/108126 በየካቲት 5 ቀን 2016 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/111502 በሀምሌ 4 ቀን 2016 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/111502 መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ክልል ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 279 የሆነ ቤት በይዞታ መለያ ቁጥር AA000021001258 በእነ ዶ/ር ዮናስ ቢርመታ አድነው (9ሰዎች) ስም የተመዘገበ ካርታ ያለው የይዞታው ስፋት በካርታቸው መሰረት 536.85 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 22,641,585.15 ( ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ አምስት ከ15/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ በግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደምብሎባሉት አራት የሥራ ቀናቶችውስጥ ባለመብቱለማስጎብኘት በሚመርጧቸውሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። የፍ/አፈዳይሮክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-28
  • Publishing entity: Federal Court Judicial Procedure Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 27, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders