የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ስንዱ ደገፋ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ንጋቱ አፍራስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.333136 በ26/06/2017 ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.136054 በቀን በ25/11/2016 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ.145518 በቀን 03/07/2017 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.145518 በቀን 27/04/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 942 የካርታ ቁጥር ወ1/ውዝ01/1703/32188/00 የሆነ የቦታ ስፋት 1272.34 ካ/ሜ ሲሆን በይዞታው በሰፈሩ ስም ኢትዮጵያ በኪራይ ውል የተያዘው 145.2 ካ/ሜ በብሎኬት የታጠረ ሲሆን ይዞታው ለመኖሪያ እና ለድርጅት የሆነ የሐራጅ መነሻ 44,126,633.16 (አርባ አራት ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ሶስት ከ16/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮያ ንግድ ባንከ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 27, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.