አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ ፎረም ህንጻ ያሉ ቦታዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች (ለመፃህፍት ቤት፣ ለስቴሽነሪ እና ለቢሮ አገልግሎት) በግልጽ ጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የንግድ ቤቶች ኪራይ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ

የግዝ መለያ ቁጥር፦ አአዩ/ብግጨ/የሱቅ ኪራይ/006/2018/26

1. የተጫራጭ ስም-

2. የተጫራች አድራሻ --- አዲስ አበባ---- ክ/ከተማ---ወረዳ--- የቤት ቁጥር---- ስልክ ቁጥር----

3. የንግድ ፈቃድ ቁጥር-----

4. ቲን ሰርተፍኬት ቁጥር..

5.የስራው አይነት...

6. የሚጫረቱበት ክፍል ቁጥር…

7. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአንድ ካሬ ሜትር ዋጋ ቫትን ጨምሮ-

ማሳሰቢያ፡-

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ ፎረም ህንጻ ያሉ ቦታዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች (ለመፃህፍት ቤት፤ ለስቴሽነሪ እና ለቢሮ አገልግሎት) በግልጽ ጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከታች በተገለፀው አድራሻ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰአት ድረስ ጨረታውን ለያዘው ሰው ማሰረከብ ወይም ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡30 ሰአት ይከፈታል።

3. ከዚህ የጨረታ ሰነድ ጋር የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ቲን ሰርተፍኬት መያያዝ አለበት።

4. የጨረታ አሸናፊዎች የኪራይ ውል መዋዋል የሚችሉት ለጨረታ ባስገቡት የንግድ ፈቃድ ስም ብቻ ነው።

5. በጨረታ ያሸነፉበትን ክፍል በምንም ዓይነት ለሌላ ወገን ስም ማዞርም ሆነ ተከራይቶ ማከራየት የማይቻል ሲሆን ይህንን ለማድረግ የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ እና የኪራይ ውሉ እንደሚሰረዝ ለማሳሰብ እንወዳለን።

6. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ ይዘው በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማቅረብ አለባቸው።

8. ይህ የጨረታ መጋበዣ ሰነድ የሚያካትታቸው ዋና የሚከራዩ ቦታዎች ዝርዝር እና የሚከራይ ቦታውን የሚያሳይ ዲዛይን ይሆናል።

9. ይህ የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ታሳቢ የሚያደርገው በሀገር ውስጥ ለሚፈፀም የአገልግሎት ሽያጭ (የምክር አገልግሎት አይጨምርም) የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይሆናል።

10.ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ዋናው ግቢ የአስተዳደር ህንፃ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር፡- 314 ስልክ ቁጥር፡- 251+111243290

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-14
  • Publishing entity: Addis Ababa University
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 27, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders