የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አዉዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዩጵያ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አዉዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሀ/ አድራሻ፦ ወላይታ ሶዶ ከተማ
ለ/ የጨረታ ዓይነት ፡ ግልፅ ጨረታ
ሐ/ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች
- ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሉት 2. የደንብ ልብስ
- ሎት.3. ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 4 1ኛ ደረጃ የወለል ምንጣፍና መጋረጃ ከነገበሩ
- ሎት 5. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
- ሎት 6. የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 7. ሞተር መለዋወጫዎች
በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው
1. በዘመኑ ተጫራቾች ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በሀገሪቱና በክልሉ የግብር ሕጎች በተደነገገው መሠረት የግብርና የታክስ ግዴታቸውን የተወጡ፡፡
2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸዉ፡፡
3. ተጫራቾች የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 3% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በደቡብ ኢትዩጵያ ክልል መንግሥት ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ስም አዘጋጅተዉ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ዋናውን እና ኮፒውን ሥልጣን ባለው አካል ተፈርሞና ማህተም ተደርጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው በ16ተኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16ተኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበትየሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች ወይም ወኪሎች አለመገኘት የጨረታዉን መከፈት አያስተጓጉለዉም፡፡
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ማካተት አለማካተቱን መግለጽ ይኖርባቸዋል። ሆኖም ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ስለማካተት አለማካተቱ በግልጽ ያላመለከቱ ከሆነ የቀረበዉ ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
8. የኤልክትሮኒክስ ዕቃዎች ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒከ መገምገሚያ መስፈርቶችን በመሙላትና በተለያዩ አራት ፖስታዎች በማሸግ በፖስታዉ ላይ የፋይናንስ ኦሪጂናል እንዲሁም ኮፒ የቴክኒክ ኦሪጂናል እንዲሁም ኮፒ መሆኑን በመግለጽ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. አሸናፊ ድርጅቶች እንደ አስፈላጊነቱ ውል ከመውሰዳቸዉ በፊት መ/ቤቱ የጠየቀውን የዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
10. ተጫራቾች የሚሞሉት የዕቃ ዋጋ ላይ መለኪያና ጥራቱን ጠብቀው መሙላትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
11. በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ታግዶ የነበረ ከሆነ የዕገዳ ግዜዉን ያጠናቀቀ፡፡
12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከወጣው ጨረታ ውስጥ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና ከዚያ በላይ ዋጋ ባለው ግዥ የሚሳተፍ ማንኛውም የሀገር ውስጥ ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
13. አሸናፊ የሚሆነዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾ በሚሰጠዉ የዕቃ ግዥ ትዕዛዝ መሠረት ዕቃዎቹን በራሱ ወጪ አስከ መ/ቤቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት የማሰረከብ ግዴታ አለበት፡፡
14 ውል የሚፈጽም ማንኛውም ሰው ውል ለመፈፀም የሚያስችል የሕግ ችሎታ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡
15. በዕዳ ያልተያዘ ያልከሠረ ወይም የሥራ እንቅስቃሴውን ያላቋረጠ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴው ያልታገደ፣ ወይም በእነዚህ ምክንያቶች ተከሶ በክርክር ላይ ያልሆነ፡፡
16. የጨረታዉ አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በጽሁፍ ከተገለፀለት በኃላ ባሉት 7 ቀናት ውስጥ ውለታውን በመውሰድ ውል መፈራረም አለበት፡፡ ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይገባ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይደረጋል፡፡
17. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸዉ ማብራሪያ ከፈለጉ ከኮሚሽኑ የግዥና/ፋይ/ንብ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 046-180-1813 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችልሉ፡፡
ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቁ ነው፡፡
ወላይታ ሶዶ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
Tender details
- Deadline: 2026-05-13
- Publishing entity: የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
- Bid bond: 3%
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
- Published: Apr 28, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.