የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ አቶ አጥናፍ ታቼ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ እመቤት መንክር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/56277 28/03/2010 ዓ.ም እና በመ/ቁ 102847 በ23/3/2015 ዓ.ም በመ/ቁ 103388 በ15/2/2015 ዓ.ም በመ/ቁ 104308 በ01/06/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 214 ካርታ ቁጥር አሽ-05/18/1/5444/ አ.ካርታ በእነ እማማ ጨርቆስ ስም የተመዘገበ አዋሳኞቹ በምዕራብ መንገድ በሰሜን በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል የውስጥ ቤት ቁጥር 210፣211፣212፣ የተገለጹ ቤቶች በምስራቅ በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል 3 ውስጥ በቤት ቁጥር 189፣191፣192 የተገለጹ ቤቶች እንዲሁም በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል 4 ውስጥ በቤት ቁጥር 193፣194፣195 በደቡብ በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል 11 ውስጥ በቤት ቁጥር 215፣216፣217፣218፣219፣220፣191 የተገለጹ ቤቶች የሚያዋስኑት ሆኖ የቦታ ስፋት 216.61 ካ/ሜ ቦታው ከጠቅላላው ይዞታ 23.27 ካ/ሜ መንገድ የሚነካው ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 14,658,429.09 (አስራ አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሃያ ዘጠኝ ከ09/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 28, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.