የቤቱ ስፋት 71 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ግርማ መኮንን እና የፍ/ባለዕዳ መስፍን መኮንን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/198168 በ05/05/2017 ዓ/ም በመ/ቁጥር/202308 በ02/07/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 230 የቤቱ ስፋት 71 ካ/ሜ የቤቱ ስፋት 58 ካ/ሜ በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው 13 ካ/ሜ አጠቃላይ በፕሮፖርሸን 71 ካ/ሜ ሲሆን የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,398,214.96 (ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ ሁለት መቶ አስራ አራት ከ96/100) የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ለግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፈሳቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። የፍ/ አፈ/ዳይሮክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-06-02 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 29, 2026
- Posted at: 2026-04-29T08:42:23.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.