የኮንደሚኒየም ቤት የሐራጅ ሸያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሸያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት መዝገቡ ማንደፍሮ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ኤፍሬም ማንደፍሮ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/196915 በ06/02/2018 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/211739 በ29/3/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሸገር ከተማ በኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 01 የህንጻ ቁጥር ብሎክ 270 የወለል ቁጥር 0 የቦታው ስፋት 41.96 ካ/ሜ የሆነ እስትዲዮ ኮንደሚኒየም ቤት የመለያ ቁጥር AA0000709017182700001 ካርታ ያለው የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 733,639.55 (ሰባት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ከ55/100 ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.PO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Publishing entity: በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 30, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.