በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በአዲስ አበባ ሪጅን ስር ለሚገኘው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት መሆን የሚችል ቤት ወይም ቢሮ በክፍለ ከተማው ክልል ውስጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

Description

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ PSSSA/AAR/04/2018

በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በአዲስ አበባ ሪጅን ስር ለሚገኘው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት መሆን የሚችል ቤት ወይም ቢሮ በክፍለ ከተማው ክልል ውስጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

1. የቤቱ ሁኔታ ቪላ ወይም ፎቅ ሆኖ ቢያንስ 500 ካሬ ሜትር እና ከዚያ በላይ የመገልገያ ወለል ስፋት ያለው ክፍል/ክፍሎች ሆኖ በተጠቀሰው ካሬ ስፋት ውስጥ ወይም በፎቁ መካከል በተከራይ የተያዘ ክፍል የሌለው መሆኑ አለበት።

2. ቤቱ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ መሆን አለባቸው።

3. ቤቱ ፎቅ ከሆነ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ውሃና የኤሌክትሪክ መስመሮች የተዘረጉለት እና እንደአስፈላጊነቱ የሊፍት አገልግሎት እየሰጠ ያለ መሆን አለበት።

4. ቤቱ ራሱን የቻለ ግቢ ቢኖረውም ባይኖረውም ቢያንስ ሁለት መኪና ማቆሚያ ቦታ ያለውና በቂ መፀዳጃ ቤት ያለው መሆን አለብት።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና ፕላን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ ከሚገኘው የሪጅኑ ጽ/ቤት ዋስትና ንግድ ማዕከል ህንፃ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ በመሙላት ከላይ በተራ ቁጥር 6 ላይ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ ሰነዱን በገዙበት የሪጅኑ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነዱን አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8. የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ ልክ 3፡15 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባልተገኙበት ይሆናል።

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. 11ኛው ቀን የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

አድራሻ፡- ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ ዋስትና የንግድ ማዕከል ግራውንድ ላይ እንገኛለን።

ስልክ ቁጥር 011-111-2313

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ አበባ ሪጅን


Tender details

  • Deadline: 2026-05-14
  • Publishing entity: Public Servants' Social Security Administration
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 02, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders