መኖሪያ ቤት የቦታ ስፋት 300 ካ.ሜ እና 90 ካ/ሜ የሆነ አፓርትመንት የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ አብይ እንግዳ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ሰለሞን እንግዳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.343876 በ06/04/2018ዓ.ም እና የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ 351176 በቀን 10/06/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤት ቁጥር 286/24 የካርታ ቁጥር የካ/217/185599/07 በሟች ወ/ሮ አሸገረች መከብብ ስም የተመዘገበ መኖሪያ ቤት የቦታ ስፋት 300 ካ.ሜ የሐራጅ መነሻ 13,242,200 (አስራ ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ አርባ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል. የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
2ኛ በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 10 የቤት ቁጥር 5-2-1 የካርታ ቁጥር ቦሌ 10 1/88/1/8/30146/48248/02 በሟች ወ/ሮ አሽገረች መክብብ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ የቤት ስፋት 90 ካ/ሜ የሆነ አፓርትመንት የሆነ ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ 6,946,020( ስድስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ስድስት ሺህ ሃያ ብር) የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም C.PO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-05
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-05 10:30
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 03, 2026
- Posted at: 2026-05-04T08:41:45.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.