ጳጉሜን አስጎብኚና የጉዞ ወኪል አ.ማ ያገለገሉ መኪናዎችን በግልጽ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የመኪና ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ማስታወቂያ

ጳጉሜን አስጎብኚና የጉዞ ወኪል አ.ማ ያገለገሉ መኪናዎችን በግልጽ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት:-

1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቶች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ::

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) ለእያንዳንዱ መኪና የጨረታ ማስረከቢያ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

3. ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል 22 ማዞሪያ አክሱም ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ኮሜት ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ከጠዋቱ 3:00 እስከ 11:00 መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራጮች ከአንድ በላይ መኪና መግዛት ከፈለጉ ዋጋ የሚያቀርቡት ለእያንዳንዱ መኪና ነው።

5. ተጫራቾች ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በቢሮ ቁጥር 107 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4:30 ሰዓት በኩባንያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።

9. ተጫራቾች መኪናዎቹን በኩባንያው የመኪና ማቆሚያ ቦታ ከሰኞ ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።

10. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ተሽከሪካሪዎች ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለው በመክፈል አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው 10 (አስር) ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል:: ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።

11.የጨረታው አሸናፊ ላሸነፈበት ተሽከርካሪዎች ከስም ማዘዋወሪያ ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን በራሱ የሚሸፍን ይሆናል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሚሸጡ መኪናዎች ዝርዝር

.

የመኪና ዓይነት

ሞዴል

የምርት ዓመት

ሻንሲ ቁጥር

 

ሞተር ቁጥር

 

ታርጋ ቁጥር

ምርመራ

 

1

ዩቶንግ ዘመናዊ የቱሪስት አውቶቡስ

ZK6122Hg

 

2017

LZYTATF61H1060824

L360-78521784

ET-3 -95942

 

በናፍጣ የሚሰራ

2

ዩቶንግ ዘመናዊ የቱሪስት አውቶቡስ

ZK6122Hg

 

2017

LZYTATF63H1060825

 

L360-78521783

ET-3--95943

በናፍጣ የሚሰራ

አድራሻ:- 22 ማዞሪያ አክሱም ሆቴል አጠገብ ኮሜት ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107

ለበለጠ መረጃ:- 09 44 00 77 22/ 09 30 79 44 44 በስራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ጳጉሜን የኢትዮጲያ መልዕክና ድርሳን!


Tender details

  • Deadline: 2026-05-15
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-15 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4:30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Pagumen Tour and Travel Share Company
  • Bid bond: 300,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: May 03, 2026
  • Posted at: 2026-05-04T09:30:54.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders