አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 1153 እና 011 515 0711 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

.

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት

የቦታው ስፋት በካ.

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

የምዝገባ  ሰዓት

የጨረታ ሰዓት

ጨረታው የወጣበት ጊዜ

1

አሃዱ /የተ/የግ/ ማህበር

 

ተበዳሪው

B+G+M+5 የሆነ የንግድ ህንፃ

1695

ቦሌ14/28/2/6/ሊዝጨ0785/268161/01

/አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 14

452,762,934.15

ግንቦት 26 ቀን 2018 .

4:30-5:30

5:30_6:00

ለሁለተኛ ጊዜ

 

አቶ ልዑል ፀሀዬ አባይ

ተበዳሪው

G+2 የሆነ መኖሪያ ቤት

239

ETH0001005000-00004274946 የቦታው ልዩ መለያ ኮድ AA000051309543

 

/አበባ ከተማ፣ የካ /ከተማ፣ በአሁኑ ለሚ ኩራ /ከተማ/ወረዳ 13 /

48,444,976.27

ግንቦት 26 ቀን 2018 .

8:30-9:30

9:30-10:00

ለመጀመሪያ ጊዜ

 


Tender details

  • Deadline: 2026-06-03
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-06-03 16:00
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 03, 2026
  • Posted at: 2026-05-06T05:36:13.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders