ኦሮሚያ ባንክ ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የጨረታዉ ቀን፣ ሰዓት፣ የሚካሄድበት ቦታ |
ጨረታው የወጣው |
||
|
ከተማ፣ ክ/ከ/ ወረዳ/ቀበሌ |
የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር |
የቦታ ስፋት በካ.ሜ/ሄክ |
||||||||
|
1 |
አቶ ጥበቡ ፈለቀ እንዳሻው |
ተበዳሪው |
የመኖሪያ ቤት (G+2) |
ሀዊ |
አዲስ አበባ፤ ቦሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 12፣ ቡልቡላ 40/60 ኮንዶሚኒየም አካባቢ |
ቦሌ12/51/5/3/ሊዝ/ዕጣ/635/7449/26992/02 |
173 ካ.ሜ |
16,743,573.83 |
በ26/09/2018 ዓ.ም ከ 3፡00-4፡00 ሰዓት በዋና መ/ቤት |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|
2 |
አቶ ጥበቡ ፈለቀ እንዳሻው |
ተበዳሪው |
የመኖሪያ ቤት(G+1) |
ሀዊ |
አዳማ ከተማ፣ ቀበሌ 01 |
6662/96 |
430 ካ.ሜ |
6,094,046.03 |
በ27/09/2018 ዓ.ም ከ 4፡00-5፡00 ሰዓት በአዳም ከተማ |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|
3 |
አቶ አካኩ አበራ ጩዌ |
ተበዳሪው |
የመኖሪያ ቤት |
አዶላ |
ጉጂ ዞን አዶላ ከተማ፤ ኦዳ አዶላ ቀበሌ |
3076/12 |
227 ካ.ሜ |
1,768,741.71 |
በ27/09/2018 ዓ.ም ከ 4፡00-5፡00 ኦሮሚያ ባንክ አዶላ ቅርንጫፍ ውስጥ |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
- ተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አካባቢ አምራን ሆቴል ጎን የኦሮሚያ ባንክ ህግ አገልግሎት ቢሮ የሚገኝበት ናትሩት ሀውስ (ህንፃ) 9ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ የጨረታ አዳራሽ ውስጥ እንዲሁም ተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በአዳማ ከተማ አራዳ አካባቢ በሚገኘው የኦሮሚያ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት የሚገኝበት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ አዳራሽ ውስጥ ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል። ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል።
- የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል። የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል።
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል። ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
- ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 1372 እና ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት ወይም ለተራ ቁ.1 እና 2 በ 011 4/67-1158/06-63 ኦሮሚያ ባንክ ሀዊ ቅርንጫፍ፤ ለተራ ቁ. 3 በ046-335 0383/84 ኦሮሚያ ባንክ አዶላ ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-04 11:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: May 03, 2026
- Posted at: 2026-05-06T05:40:02.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.