ወጋገን ባንክ አ.ማ. የንግድ ህንጻ (B+G+6+ ቴራስ) በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ወጋገን ባንክ አ.ማ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር፡ ወጋገን 022/2018
ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የንብረቱ አድራሻ |
የቦታው ስፋት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር |
የንብረቱ ዓይነት/የይዞታው አገልግሎት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታው የሚከናወንበት ቀን |
||
|
ከተማ/ ክልል |
ክ/ከተማ/ከተማ/ዞን |
ወረዳ/ ቀበሌ |
|||||||||
|
1 |
ቴዎድሮስ ታደሠ እና አቢሲንያ የቄራ አገልግሎ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር |
አቶ ቴዎድሮ ታደሰ |
በቅሎ ቤት |
አዲ አበባ |
የካ |
13 |
1,012 ካ.ሜትር |
AA000051308702 |
የንግድ ህንጻ (B+G+6+ ቴራስ) |
179,473,281.05 |
ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጧቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
- በጨረታው ላሸነፈ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ እንዲሁም ተጨማሪ የመያዛ ንብረት ለሚያቀርቡ ተጫራች፣ ባንኩ በብድር መመሪያ መሰረት ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት፣ ከጧቱ 3፡00 – 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው። ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል።
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል
- ጨረታው የሚካሄደው በወጋገን ባንክ ዋና መስርያ ቤት ህንፃ 13ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይሆናል።
- ለሀራጅ ጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
- ተበዳሪው /ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ተበዳሪው /ንብረት አስያዡ/ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል። ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው።
- ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል።
- ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት 011-558-1837፣ መደወል ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ወጋገን ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-06-02 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Wegagen Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: May 03, 2026
- Posted at: 2026-05-06T06:24:53.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.