የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር FA- 10/2025/26
የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የተለያዩ አቅም ያላቸው ጀነሬተሮች፣ ካዝናዎች ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ዩፒኤሶች፣ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣ የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች (የመሽ ወንፊት፣ የፋቢሪክ እና የቆዳ)፣ ጠረጴዛዎች፣ የብረት ፋይል ካቢኔቶች፣ ካዉንተር እና ኬጂ ከነ ጥበቃ ቤቶች እና ከሌሎች ቁርጥራጭ ብረቶች ጋር፣ አሉሚኒየም ፓርትሽኖች፣ የቅርንጫፍ ማስታወቂያ ታፔላዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች፣ የተቃጠለ የመኪና ዘይት ከነ በርሜሎቹ ጋር፣ አሮጌ ጋዜጣዎች፣ ባዶ የቶነር እቃዎች፣ የሽንት ቤት መቀመጫዎች እና የእጅ መታጠቢያ ሲንኮች፣ የወለል የፕላስቲክ ታይልስ፣ ኮሪደሮች እና በረንዳ ላይ የሚቀመጡ የአበባ ማሳደጊያ ሳህኖች እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል:
1. የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ከሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም የግብር መለያ ካርድ ያላችሁ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ኢጆ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ላገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ መንገድ ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ፊትለፊት፣ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
2. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የከፈሉበትን ስሊፕ እና የጨረታ ሰነዱን በመያዝ ሱሉልታ አካባቢ ሁለት ቦታ በሚገኙት የባንኩ መጋዘኖች ሹፉኔ ቻይና ጋራጅ 100 ሜትር ገባ ብሎ አነን ሰላሌ የወተት ማቀነባበሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ እና ሱሉልታ አዲስ የተሰራዉ ክ/ከተማ ከዋና መንገዱ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ፒልከን ተብሎ በሚታወቀው የባንኩ ግምጃ ቤት ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ግንቦት 3፣ 5 እና 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧት 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ።
3. እንዲሁም የተቃጠለ የመኪና ዘይት ከነበርሜሉ ያለበትን ሁኔታ ለመጎብኘት ቄራ በረት ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ጎፋ በሚወስደው ዋናው መንገድ 100 ሜትር እንደተጓዙ በቀኝ በኩል የባንኩ ጋራጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በማንኛውም የሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት ድረስ መጎብኘት ይችላሉ።
4. ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ መንገድ ራንግ ህንጻ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ።
5. ባንኩ የሚከተለው የማወዳደሪያ ዘዴ በሰነዱ ሰንጠረዥ ላይ ንብረቶቹ እንደተዘረዘሩት ዓይነት በተናጠል መስመር በመስመር ሲሆን ባንኩ የተሻለ ሆኖ ካገኘም በጥቅል ወይም በጅምላ ያወዳድራል።
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ዉን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ በተጨማሪም የጨረታ መነሻ ዋጋ ለሌላቸው የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
8. ተጨራች የሚገዛበት የመግዣ ዋጋ በግልጽ በዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% መካተቱን ወይም አለመካተቱን ለይቶ መጻፍ ይኖርበታል፤ ነገር ግን አሻሚ ቦታ ላይ ወይም ሁለቱም ቦታ ላይ ተመሳሳይ ዋጋ ከጻፈ እና ምንም ካልተገለጸ ባንኩ የቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተካቶ እንደቀረበ ታሳቢ ያደርጋል።
9. አሸናፊ መሆናቸው የተገለፀላቸው ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያውን በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፖኦ ውርስ ይደረጋል።
10. ጨረታው ሰኞ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ሰኞ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
11. ባንኩ የተሸለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)
ስልክ ቁጥር 011 557 6174 ፖ.ሣ.ቁ 16936
ማህበረሰቡን ማጎልበት፣ ህይወትን መለወጥ!
Tender details
- Deadline: 2026-05-18
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-05-18 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Cooperative Bank S.C.
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 03, 2026
- Posted at: 2026-05-06T07:14:59.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.