ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ግርማ አለባቸው ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የካርታ ቁጥር ኮ/ቀ/የማ/ን/መ/114/23359/00 በወ/ሪት ፈትያ አብራር ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን B+G+5 የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ግርማ አለባቸው ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የካርታ ቁጥር ኮ/ቀ/የማ/ን/መ/114/23359/00 በወ/ሪት ፈትያ አብራር ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን B+G+5 የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
1. የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት ብር 72,686,825.50 (ሰባ ሁለት ሚሊየን ስድስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሀያ አምስት ብር 50/100 ሳንቲም) ነው።
2. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ) በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ መስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱን መመስረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፤ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል።
4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል።
5. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊው በ15 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ያሆናል።
6. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ይመለስላቸዋል።
7. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ይሸፍናል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዡ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
8. ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
9. ጨረታው ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክ/ከተማ ልዩ ስሙ ሰንጋተራ ከባንኩ ዋናው መ/ቤት 9ኛ ፎቅ ላይ ይደረጋል።
10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 74 43 43 93
Tender details
- Deadline: 2026-06-05
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: May 03, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.