የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) የመኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪዉ የብድር ዕዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) ከሥር በዝርዝር ለተመለከቱት ተበዳሪዎች ያበደረው ገንዘብ በብድር ውል መሠረት መከፈል ስላልቻሉ ባንኩ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተመለከቱትን ለብድሩ መከፈል ዋስትና/መያዣ እንዲሆን ስልጣን ባለው የመንግስት አካል የተመዘገቡትን እና ያሳገደዉን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በማሻሻያ አዋጁ ቁጥር 216/2000 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪዉ የብድር ዕዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል።

ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ሐራጁ በሚካሄድበት ቦታ እና ዕለት በመቅረብ እንዲወዳደር ተጋብዟል።

.

የተበሪው ስም

የአስያዡ ስም

የንብረቱ አይነት

አበዳሪው ቅርንጫፍ

ከተማ

/ከተማ/ ቀበሌ

የካርታ ቁጥር

የቦታው ስፋት

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ጨረታ የሚካሄድበት ቀን እና ቦታ

1

አቶ ባህሩ ገመቹ ፈይሳ

አቶ ባህሩ ገመቹ ፈይሳ

የመኖሪያ ቤት

ቢርቢርሳ

ሽገር ከተማ (በቀድሞ የሱሉልታ ከተማ)

መነ አቢቹ

Sul/2411/12

200 .

3,321,464.21

ጨረታው ግንቦት 27 ቀን 2018 . ጧዋት 400-600 ሰዓት ላይ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ . መኖሪያ ቤቱ በሚገኝበት አከባብ በሚገኝ በባንኩ ወሰርቢ ቅርንጫፍ ይካሄዳል::

ተጫራቾች እንዲያውቋቸው፡-

1. ተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 (25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ሀራጁ በሚካሄድበት አድራሻ ቀርበው በመመዝገብ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ:: ጨረታውን በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ፣ ንግድ ፈቃድና የድርጅቱን ውክልና እና የታደሰ መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት፤

2. ጨረታው ከላይ ቀንና ሰዓቱ በተገለፀው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይካሄዳል፤ ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፤

3. ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በስ.ቁ 011 126 4524/29 ወይም +251 91 244 1524፤ ላይ በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያ/መረጃ ማግኘት ይችላሉ፤

4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15(አሥራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ እንዲቀርብ ይደረጋል። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፤

5. የጨረታው አሸናፊ በሕጉ መሠረት ለመንግስት የሚከፈለውን ማንኛውንም የቫት(ካለ) እና ታክስ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን ከፍሎ ስሙን ወደ ራሱ እንዲዛወር ያደርጋል፤

6. ባንኩ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-06-04
  • Publishing entity: Oromia Cooperative Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 03, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders