የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ንብረትነታቸው የኮሚሽኑ የሆነና በድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ተከማችተው የሚገኙ ቁርጥራጭ ብረታ ብረትና የብረታ ብረት ውጤቶችን ባሉበት ሁኔታ ከፌዴራል የገንዘብ ሚ/ር የተሰጠ የመነሻ ዋጋን መሰረት በማድረግ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ቁርጥራጭ ብረታብቶችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ንብረት ነታቸው የኮሚሽኑ የሆነና በድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ተከማችተው የሚገኙ ቁርጥራጭ ብረታ ብረትና የብረታ በረት ውጤቶችን ባሉበት ሁኔታ ከፌዴራል የገንዘብ ሚ/ር የተሰጠ የመነሻ ዋጋን መሰረት በማድረግ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1.በጨረታው ላይ የሚወዳደሩት በማዕድን ሚ/ር የተለያዩ ብረት አቅላጭ የግል ድርጅት የሆኑና የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና መታወቂያ ማቅረብ የሚችሉ ናቸው፡፡
2. ተጫራቾች ፒያሳ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አጠገብ በሚገኘው የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከቢሮ ቁጥር 105 መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ብረታ ብረቶቹን ድሬድዋ ማረሚያ ቤት ማዕከል መሆኑን ተገንዝባችሁ ንብረቶቹ ያሉበትን ሁኔታ በአካል ተገኝቶ መመልከት የሚቻል ሲሆን ለምልከታው ቀድማችሁ ፕሮግራም በማስያዝ የንብረቶቹን ይዞታ ማየት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡
4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ቁርጥራጭ የብረት ዓይነት የጨረታ መነሻ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከመዝጊያው ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው።
5. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የተዘጋጀ መሆን አለበት፡፡
6. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡ ይሁን እንጂ የብረታ ብረቶቹን ግምታዊ ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ዋስትና ያላስያዘ እንዲሁም በሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ የግዥ/ን/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 407 ይከፈታል። ነገር ግን በጨረታው መክፈቻ ቀን ኮሚሽኑን ከአቅም በላይ የሆነ ጉዳይ ከገጠመው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ጨረታው እንዲከፈት ይደረጋል። ቅዳሜና እሑድ እንዲሁም በብሔራዊ በዓል ቀን የጨረታ ስነ-ስርዓት አይኖርም። ይሁንና ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት እለት ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን አከፋፈት ስነ-ስርዓት አያስቀረውም።
8. ጨረታውን አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው 7(ሰባት) የሥራ ቀናት በኋላ በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ ክፍያ ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ውርስ ተደርጎ ለመንግሥት ገቢ እንዲሆን ይደረጋል።
9. ጨረታውን አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ብረታ ብረቶች ሙሉ ክፍያ ፈፅመው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
10. ተጫራቾች ያሸነፉትን ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን ብረታ ብረቱ ከሚገኝበት ስፍራ ቅርብ በሆነ የመንግሥት የምድር ሚዛን በማስመዘን ፕሪንት አውት በማቅርብ ውል በፈረሙ በ15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ቁርጥራጭ ብራታ ብረቶቹን በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው። ግምታዊ መጠኑ ከፕሪንት አውት ከሚገኘው ትክክለኛ የብረቱ መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት የሚኖረውን ልዩነት ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን ገዥው በትርፍ የሰጠው ገንዘብ ካለ በኮሚሽኑ ተመላሽ ይደረጋል።
11. ኮሚሽኑ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይደረጋል።
12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
13. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ወይም ሌላ ጨረታውን ለመሰረዝ የሚያበቃ ምክንያት ካጋጠመው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ፒያሳ ፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ዋና መ/ቤት ከአዲስ-አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍ ብሎ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-23-27-37-67/0923777077/0911334834 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
Tender details
- Deadline: 2026-05-20
- Publishing entity: Federal Prisons Commission
- Bid bond: 10% ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 05, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.