የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

Description

የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

1. አድራሻ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም መስተዳደር ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ፣ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በ2018 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።

ስለዚህ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

2. የጨረታ ቁጥር ብቸ/17/2018

3. ጨረታ ዙር 17ኛ

4. የጨረታው አይነት መደበኛ ጨረታ

5. የመ/ቤት ስም ብቸና ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት

6.የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ በማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ እና በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተለጠፈበት ቀን ባሉት 10/ አስር/ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው በእለቱ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል።

7. ጨረታው የሚከፈተው ከጨረታው የመጨረሻ ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ብቸና ከተማ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሸ ትልቁ አዳራሸ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከተመሰከረለት ባንክ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከ15% /አስራ አምስት ፐርሰንት/ ያላነሰ сро /ሲፒኦ/ማቅረብ ይኖርበታል።

9. አሸናፊው ተጫራች ካቀረበው አጠቃላይ የሊዝ ዋጋ ለመኖርያና ለንግድ ቦታ ከ15% /አስራ አምስት ፐርሰንት ያላነሰ ቅድመ ክፍያ ማቅረብ አለበት።

10. ተጫራቹ የዋጋና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላት ፡- ኦርጅናል ሲፒኦ እና የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ በአንድ ፖስታ፣ የተሞላውን አንድ ኦርጅናል ሰነድ በአንድ ፖስታ፣ አንድ የተሞላ ኮፒ ሰነድ በአንድ ፖስታ በማሸግና ሦስቱን ፖስታዎች በአንድ ላይ በሌላ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በታሸገው ኤንቨሎፕ ፖስታ ላይ የተጫራቹን ስም፣ የቦታውን ልዩ ኮድ እና የጨረታ ቁጥር በግልጽ በመጻፍ ለቦታው በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

11. ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገልጸው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።

12. ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

13. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይምሲፒኦ የሚመለስበትን ጊዜ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል።

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ሲፒኦ ሲያሰሩ በብቸና ከተማ አስ/ መሬት ጽ/ቤት መሆን አለበት።

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በ0586651701/003/ ደወሎ መጠየቅ ይቻላል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን መስተዳድር ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት 


Tender details

  • Deadline: 2026-05-15
  • Publishing entity: በምስራቅ ጎጃም ዞን መስተዳድር ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት
  • Bid bond: 15%
  • Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published: May 05, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders