የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨቁ 13/2018 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ዘርፍ |
የጨረታዉ ዓይነት |
ዕቃው ያለበት ቦታ |
|
1 |
የፅዳት ዕቃዎች |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
2 |
ምግብ ነክ ዕቃዎች |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
3 |
መለዋወጫዎች |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
4 |
ኮስሞቲክስ |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
5 |
ጫማ |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
6 |
ኤሌክትሮኒክስ |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
7 |
ፓኪንግ ማሽን |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
8 |
የኮስሞቲክስ ዕቃዎች |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
9 |
ፈሳሽ ኬሚካል |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
10 |
ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶች (west scrap material |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-
1. በጨረታው ሽያጭ ሥርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ስብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም። በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፤
2. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00- 5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ግቢ ዉስጥ ውርስ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋና አምስት በመቶ (3) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ኮስሞቲክስ ዕቃዎች (ምድብ 01) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፤ (ምድብ 02) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) ፤(ምድብ 3) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ)፤ ጫማ (ምድብ ዕ) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፣ (ምድብ 2) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ)፤ ፈሳሽ ኬሚካል ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር)፣ ኤሌክትሮኒክስ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር)፣ ቁርጥራጭ ብረት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ፓኪንግ ማሽን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ |
እስከ 03/09 2018 |
04/09/2018 ዓ/ም 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 3፡45 ሰዓት ይከፈታል |
|
2 |
ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት |
ሐራጅ ጨረታ |
እስከ 03/09 2018 |
04/09/2018 ዓ/ም 4:00 ሰዓት ይከፈታል |
5. ጨረታው መክፈቻ ቦታ: በሰመራ ጉ /ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጠጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
8. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
1ዐ. የዕቃዉን ናሙና (sample) ሳያይ የሚጫረት ተጫራች ቅ/ፅ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑ ይታወቅ።
11. አሸናፊ ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) 15% የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ።
12. ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ፡- 033 240 1510 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: May 05, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.