የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ አቶ ሙሉነህ ወርቅነህ እና በፍ ባለዕዳ አቶ በድሩ አወል መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጕዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.97657 በ15/10/2009ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.126375 በቀን 04/6/2012 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ.126375 በ7/2/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በን/ስ/ክ/ከተማ ወረዳ 19 ቀበሌ 58 በአሁኑ ወረዳ 11 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 427 በቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ቁጥር 19/15747 የሆነ ካርታ የሌለው ሰነድ አልባ የቦታ ስፋት በራሳቸው ስምምነት የሰጡትን መንገድን ጨምሮ 685.85 ካ/ሜ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 8.85 ካ/ሜ ይነካዋል ቤቱ ግማሹ ለንግድ ሱቅ እና ለጋራጅ ስለሚጠቀሙበት ካፒታል ጌን ታክስ የሚከፈል ሆኖ ቤቱ ካርታ የሌለው ስለሆነ የስም ዝውውር ለማድረግ የማይቻል ሲሆን የሐራጅ መነሻ 19,418,028.25 (አስራ ዘጠኝ ሚልዩን አራት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ሃያ ሰምንት ብር ከ25 ሳንቲም) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም C.P.O አሠርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሠርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-10
- Publishing entity: የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
- Bid bond: 25%
- Published: May 06, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.