የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በመደበኛ የሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሐረሪ ክልል በተለያዩ አካባቢ የሚገኙ (1ኛ አንደኛ መንገድ አሚር ኑር ፖሊስ ጣቢያ 2ኛ- ጤና ቢሮ ፊት ለፊት : 3ኛ-ቀላዳንባ እና 4ኛ-ማልቴዝ ጀርባ ) ለንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በመደበኛ የሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሚያዚያ 28/2018 ዓ/ም እለተ እሮብ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ ቢሮ በቢሮ ቁጥር 34 ዘወትር በስራቀናት እና በስራ ሰአት መግዛት ይችላሉ፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በመግዛት ለቦታዎቹ በካሬ ሜትር የሚያቀርቡትን ዋጋ እና የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድመ ክፍያ በጨረታ ማወዳደሪያ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አደርጎ ለጨረታው ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ግንቦት 11 እለተ ማክሰኞ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰአት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በቀን 11/9/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰአት ተዘግቶ ፤በቀን 12/9/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አራተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ቦታ የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኝው ውጤት 5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ዋጋ 80 በመቶ ነጥብ ሲኖረው የቅድሚያ ክፍያ መጠን ደግሞ 20 በመቶ ነጥብ ይኖረዋል። የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሁለቱ ነጥቦች ድምር በሚገኝ ውጤት ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የቅድሚያ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ክፍያ ለንግድ ከ20 በመቶ ማነስ የለበትም።
- የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በግልፅ በይፋ ከተገለፀ በኃላ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
- ቢሮው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0919 121 917 ወይም 0910 415 925 ዘወትር በስራ ሰአት በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ድህረ-ገፅ https://www.hararilanddev,gov.et ወይም ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ማግኘት ይችላሉ።
የሐረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-05-19
- Publishing entity: Harari Regional State Urban Development and Construction Bureau
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published: May 06, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.