የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት መምሪያ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያ ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለመግዛት ካቀዳቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያ ግዥዎች ውስጥ
- 1ኛ. ዲሰክቶፕ ኮምፕዩተር በቁጥር 02፣ ላፕቶፕ በቁጥር 01፣ ፍለሽ በቁጥር 15፣
- 2ኛ. ፕሪንተር ኢንክ በቁጥር 40 ሆኖ 26 A ብዛት 5፣ 80 A ብዛት 22፡ 59A ብዛት 13፣ የፕሪንተር ወረቀት A4/80 ግራም/ በደስታ 200፣ ሰማያዊ ቢክ እስክርቢቶ /ኦርጅናል ሰማያዊ /በባኮ 20 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- ያቀረቡት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ለተራ ቁጥር 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ለተራ ቁጥር 2 የጽህፈት መሳሪያ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግዥው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት የሚቻል ሲሆን የሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ነው።
- በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ለተራ ቁጥር 1 ብር 6,000 (ስድስት ሽህ ብር) ለተራ ቁጥር 2, ብር 5000 (አምስት ሽህ ብር) በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብን ማስያዝ አለባቸው።
- ጨረታ ሳጥን በግዥ ፋይናስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ይገኛል።
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 14 ይገኛል።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል። ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር መሆኑን እንገልጻለን። የእያንዳንዱን ሎት ሁሉንም ዝርዝር ያልሞላ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ የሞላበትን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለበት።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጐ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የመጨረሻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
- 2014 ዓ/ም የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ያወጣውን አዲስ የተሻሻለ የግዥ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 0058 /058 141 0091 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-19
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-19 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Debre Tabor City Administration City & Urban Development Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 04, 2026
- Posted at: 2026-05-07T06:25:59.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.