በፀደይ ባንክ ፍ/ሰላም ዲስትሪክት አቶ እንየዉ እሸቴ ቆያቸዉ በፀደይ ባንክ ይልማና ዴንሳ ቅርንጫፍ የተበደሩትን ብድር በዉሉ መሰረት መመለስ ስላልቻሉ ለብድሩ አመላለስ በመያዣ የተያዙትን ቤቶች በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በፀደይ ባንክ ፍ/ሰላም ዲስትሪክት አቶ እንየዉ እሸቴ ቆያቸዉ በፀደይ ባንክ ይልማና ዴንሳ ቅርንጫፍ የተበደሩትን ብድር በዉሉ መሰረት መመለስ ስላልቻሉ ለብድሩ አመላለስ በመያዣ የተያዙትን በተበዳሪዉ ስም የተመዘገቡ ከዚህ በታች በአዋሳኝ የተገለፁትን ቤቶች በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡
1ኛ.በአቶ እንየዉ እሸቴ ቆያቸዉ ስም የተመዘገበ እና በአዴት ከተማ 04 ቀበሌ ልዩ ስሙ ጋፋት የሚገኝ የካርታ ቁጥር ከአገ/118149/15 የሆነ በአዋሳኝ በሰሜን ተመስገን፣ በደቡብ መንገድ፣ በምሥራቅ ጀማል ሲራጅ እንዲሁም በምዕራብ እንድሪስ ሁሴን የሚዋሰን እና የቦታዉ ስፋት 150 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ግምት ብር 1,786,364.03 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማንያ ስድስት ሽህ ሶስት መቶ ስልሳ አራት ብር ከዜሮ ሶስት ሳንቲም) ይጫረታል፡፡
2ኛ.በአቶ እንየዉ እሸቴ ቆያቸዉ ስም የተመዘገበ እና በአዴት ከተማ 03 ቀበሌ ልዩ ስሙ ጤና ጣቢያ የሚገኝ ካርታ ቁጥር ከአገ/114040/14 የሆነ በአዋሳኝ ሰሜን መንገድ፣ በደቡብ 88 ቁጥር፣ በምሥራቅ አሰፋ ሀይሉ እንዲሁም በምዕራብ 94 ቁጥር መካከል የሚገኝ የቦታ ስፋት 150 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ግምት ብር 796,549.09 (ሰባት መቶ ዘጠና ስድስት ሽህ አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከዜሮ ዘጠኝ ብር ሳንቲም) ይጫረታል፡፡
1. ጨረታው ግንቦት 26/2018 ቀን ከረፋዱ 3፡00 እስከ 6፡00 ባለዉ ጊዜ ከፍ ብሎ በተገለፀዉ መነሻ ዋጋ ይጫረታል፡፡
2. ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ አዴት ከተማ የሚገኘዉ ፀደይ ባንክ ይልማና ዴንሳ ቅርንጫፍ ነው፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋዉን 1/4 በፀደይ ባንክ ማንኛዉም ቅርንጫፍ የተረጋገጠ ሲፒኦ በመያዝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ይዘዉ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ ማንነታቸዉን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘዉ መቅረብ አለባቸዉ፡፡
5. ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ የሚጫረተዉ ሰዉ ዉክልና እና የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
6. ለመንግስት የሚከፈል ማንኛዉም ግብር ቫትን ጨምሮ እንዲሁም ከመንግስት የሚጠየቅ የሊዝም ሆነ ከቦታዉና ቤቱ ዝዉዉር ጋር የተያያዘ ማንኛዉም ክፍያ በተጫራች /በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
7. የጨረታ አሸናፊዉ ጨረታዉን ባሸነፈ በ15 ቀን ዉስጥ ያሸነፈበትን ሙሉዉን ገንዘብ ከፍሎ ማጠናቀቅና ቤቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
8. በ15 ቀን ዉስጥ ሙሉ ገንዘቡ ካልተከፈለ የተያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ እንደገና ይወጣል፡፡
ፀደይ ባንክ ይልማና ዴንሳ ቅርንጫፍ
Tender details
- Deadline: 2026-06-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-06-03 12:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Bid bond: 25%
- Published: May 04, 2026
- Posted at: 2026-05-07T10:58:43.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.