የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ተፈሪ ገብረመስቀል (8 ሰዎች) እና በፍ/ባለዕዳ የትናየት ሀይለመስቀል መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.335150 በ30/05/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ.335528 በ26/03/2018ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት በቀድሞ ቦሌ ክ/ከተማ በአሁኑ ለሚኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 10 የቤት ቁጥር አዲስ ካርታ ቁጥር ቦሌ/48/9/2/4812/00 የሴሪ ቁጥር 027543 እና የመዝገብ ተራ ቁጥር 4812 የተመዘገበ የቦታ ስፋት 94.64 ካ/ሜ የሆነ ቤት ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 7,662,283.36 (ሰባት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ ሶስት ከ36/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ ቤት/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ዳ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-11
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-11 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 07, 2026
- Posted at: 2026-05-07T12:35:32.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.