የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወ/ሮ የሮምነሽ ተገኝ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ አሸናፊ ጉጃ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.85630 በ11/08/2014ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.88689 በቀን 21/11/2014ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.88689 በቀን 20/3/2015ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት
1ኛ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 450 ቁጥር 18/72/25/046/00 የተመዘገበ ተነጻጻሪ ካርታ ያለው ጠቅላላ የቦታ ስፋት 749 ካ/ሜ ቤቱ ያረፈበት 344.72 ካ/ሜ ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው 217.28 ካ/ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደረሰው የቦታ ስፋት 562 ካ/ሜ ከጠቅላላው ይዞታ ላይ የመንገድ ጥናት 97 ካ/ሜ ይነካዋል ይዞታው LDP Relocaion site ለመልሶ ማስፈሪያ የተያዘ የሐራጅ መነሻ 14,011,646 (ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
2ኛ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 451 ካርታ ያለው ተነጻጻሪ ካርታ ያለው ጠቅላላ የቦታ ስፋት 538 ካ/ሜ ቤቱ ነገር ግን በቀን 10/07/2004 ወጪ የሆነው ካርታ በፕሮፖርሽን ያደረገው በመሆኑ ቤቱ ከጠቅላላው በፕሮፖርሽን የሚደርሰው 187ካ/ሜ ከጠቅላላው ይዞታ ከቤት ቁጥር 450 እና 451 ላይ የመንገድ ጥናት 97 ካ/ሜ ይነካዋል። ይዞታው LDP Relocaion site ለመልሶ ማስፈሪያ የተያዘ የሐራጅ መነሻ 7,015,371 ( ሰባት ሚሊዮን አስራ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ አንድ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-11
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ሰአት በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-11 11:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ሰአት በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 07, 2026
- Posted at: 2026-05-07T12:37:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.