የቤት የሐራጅ ሸያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሜ የወጣ የሐራጅ ሸያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አቶ ሙራድ ሺፋ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ድንቃ ተሊላ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/10512/5 በ01/08/2016ዓ.ም ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/112106 በ04/11/2016ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 160 የሆነ ካርታ የሌለው ነገር ግን ደብተር ያለው ጠቅላላ የይዞታ ስፋት የሌሎቹ ግቢው ውስጥ ያሉ ቤቶች ጨምሮ 159.86 ካ/ሜ የቤቱ ስፋት ፍርድ ያረፈበት ቤት ስፋት 47.22 ካ/ሜ በፕሮፖርሽን ለቤቱ ለግቢው የሚደርሰው 7.56 ካ/ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን (ተነጻጻሪ) የፍ/ባለመብት እና የፍ/ባለዕዳ ድርሻ 54.78 ካ/ሜ የሆነው የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,848,718.94 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ አስራ ስምንት ከ94/00) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.112106 በቀን 27/5/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ 1/4ኛ 712,179.73 ( ሰባት መቶ አስራ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ መቶ ከ73/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍ/ቤት የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-11
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-06-11 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Court Judicial Procedure Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 08, 2026
  • Posted at: 2026-05-08T07:24:55.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders