የቤት ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የመ.ቁ. 106345

ቀን 29/07/2017

በፍ/ባለመብት እነ ወ/ሪት ሊና መሀመድ ሃሩን እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ደብሮ በከር /8 ሰዎች መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 102648 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 03 ክልል በሟች መሀመድ ሃሩን ዋሬ ስም በካርታ ቁጥር 22 የተመዘገበ የቤት ቁጥር 128 የሆነ በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1,755.636.33 አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ስድስት ብር/33/100/ በሆነ ዋጋ በሃራጅ ሽያጭ እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል። ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 4፡30 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሔድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡35 እስከ 5፡20 ባለው ጊዜ ይከናወናል።

በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ማንኛውም ተጫራች ለሃራጅ ጨረታው ከመመዝገቡ በፊት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ቀድሞ በCPO በባንክ አስይዘው እንዲመዘገቡ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ በCPO ወይም በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው። ቀሪውን 3/4ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል።

የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር ችሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-30
  • Bid closing time: 10:35
  • Bid opening: 2026-05-30 10:35
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Federal First level Court
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 06, 2026
  • Posted at: 2026-05-08T09:20:13.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders