በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የግልፅ ጨረታ ቁጥር 06/2018

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

በግልፅ ጨረታ ቁጥር 06/2018 በ11/09/2018 ዓ.ም ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፣

ስለዚህ በጨረታ የቀረቡት ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን መጫረት የሚፈልግ ተጫራች -

1. "ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ዲጅታል /ብሔራዊ መታወቂያ ያለው

2. ለጨረታ የቀረበው ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ሲሆን የሚገኘው ድሬዳዋ ሙዲአነኖ ግቢ በሚገኘው ተሽከርካሪ መጋዘን ውስጥ ነው።

3. የተሸከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የሆነ ሰው በጨረታ መሳተፍ አይችልም።

4. በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት በመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከ01/09/2018 ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰአት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት ተሽከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል።

5. ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።

6. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድሬዳዋ ሙዲአነኖ የሚገኘው ገቢ ውስጥ ነው።

7. ተጫራቾች ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆነ አለበት።

8. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ለመግዛት ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 5% በንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ የሞሉትን የጨረታ ሰነድ እና ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማያያዝ በዕለቱ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 3:45 ድረስ በድሬዳዋ ሙድአነኖ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

10. ጨረታው ከጠዋቱ 3፡50 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ጉምሩክ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ሳጥኑ ይከፈታል።

11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፈለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

12. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሽከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል፣

13. ከላይ በተራ ቁጥር 12፡00 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሽከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስረከቢያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።

14. የጉምሩክ ኮምሽን ድ/ዲ/ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915 460 970 (0912 885 746 ) መደወል ይቻላል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-19
  • Bid closing time: 09:45
  • Bid opening: 2026-05-19 09:50
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: May 09, 2026
  • Posted at: 2026-05-09T08:25:59.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders