Vehicle and machinery sale
የአገዉ ግ/ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ጀኔሬተር በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአገዉ ግ/ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በድርጅቱ የዉሃ መገኛ ቦታ ላይ የሚገኘዉን ጀኔሬተር በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ዝርዝር መግለጫ በተቀመጠዉ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸዉ።
- ጨረታዉ ለማንኛዉም ተጫራች ክፍት ነዉ።
- የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ከመጫረቻ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጨራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢንድ ቦንድ) ለሚወዳደሩት ከጠቅላላ ዋጋ የሚመለስ 5 በመቶ ብር 151,875 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዮ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ። በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በድርጅታችን ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታዉ ፖስታ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- የመጫረቻ ሰነዱን አገዉ ግ/ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ገቢ ግዥ፣ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት 300 (ሶስት መቶ) ብር ከፍለዉ መግዛት ይችላሉ።
- የመጫረቻ መነሻ ዋጋ 3,037,500 (ሶስት ሚሊየን ሰላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር ) ሲሆን ዝርዝር መግለጫዉ በሰነዱ ላይ ያለ በመሆኑ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታዉ ከወጣበት ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ በስራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን 4፡00 ታሽጎ ከጥዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበትና ባይገኙም ጨረታዉ ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ሙሉ ክፍያዉን ዕቃ እስካለበት ቦታ ድረስ ዕቃዉን መረከብ እና ክፍያ በባንክ ገቢ የተደረገዉን ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርበታል። በተጠቀሰዉ ቀን ክፍያ ባይፈጽሙ የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ የሚጠቀም መሆኑን እንገልጻለን።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
- አሸናፊው የሚለየው ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ብቻ ነዉ።
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 224 0462 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።
የአገ/ግ/ቤት/ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-18 10:15
- Region: Amhara
- Publishing entity: Agew Water and Sewerage Authority
- Bid bond: 5 በመቶ ብር 151,875
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T09:14:26.000Z